በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ል...

image description
- In Uncategorized    7

በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት ጥራት ማረጋገጫ ዝርዝርን/Specification/ አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት ጥራት ማረጋገጫ ዝርዝርን/Specification/ አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

ምገባ ኤጀንሲ ፣ጥር 13/2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ

።።።።።።።።።።።።።።።።።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ በ2017 የትምህርት ዘመን በተማሪዎች የደንብ ልብስ ዝግጅት የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ ዝርዝር ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል ፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዩ መሀመድ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ፣ ፋይናንስ ቢሮ ፣ የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ፣ ጨርቃጨርቅ ኢንስቲትዩት ፣ ቴክኒክና ሙያ ፣ አምራች ድርጅቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ የግብዓት ዘርፍ ምክትል/ዋና ዳይሬክተር አቶ ምነውር ኑረዲን፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚዘጋጀውን የተማሪዎች የደንብ ልብስ በተሻለ የጥራት ደረጃ ለማዘጋጀት በተዘጋጀው የጥራት ማረጋገጫ ዝርዝር ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን በመጥቀስ በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ውይይቱ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ አስቀምጠዋል ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments