የፕሮጀክትና ዝግጅት ፣ጥናትና ግብዓት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት
Directorate Director
ምነወር ኑረዲን አብራር

ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ ፕሮጀክት ማዘጋጀት እና ግብዓት ማፈላለግ ፤ የፕሮጀክት አፈፃፀም ክትትል ድጋፍና ግምገማ ማካሄድ
Directorate Director's Message
ለተማሪዎች ልዩ ዕድል ፈጥሮ ባዶ ምሳ ዕቃ ያስጣለ፣ ለወላጆች እፎይታ ሆኖ ልጆቻቸውን ሁሉ ወደ ት/ ቤት እንዲልኩ ያደረገ፣ ለመምህራን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ለመማር ማስተማር ሥራው የሚያግዝና ት/ቤት የሚወደድ ቦታ እንዲሆን ያስቻለ፣ በተመሳሳይ የትምህርት ግብአትና የደንብ ልብስ ስለሚመገቡት ነገር ምንም ሳይጨነቁ ሃሣባቸውን ሁሉ ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲሆን ያደረገው የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር! አለኝታነት፣ ወገን መሀል መኖርን እና የመሪዎችን ርህራሄ ማሳያ የሆነው ደግሞ የዕለት ጉርስ አጥተው ከቆሼ ላይ ምግብ ለማንሳት የተዘረጉ እጆችን በመሰብሰብ በተዘጋጀ ንጹህ ቦታ ትኩስ ምግብ በተገቢው የሚቀርብባቸው የተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከላት! እነዚህን ሰው ተኮር ተግባራትለመምራት በመመደቤ በጣም ደሰተኛ ነኝ! ነገ በበለፀገች ሀገር ለትውልድ የምናወርሳትን ኢትዮጵያ ዛሬ ለመስራት በወንድማማችነት /በእህትማማችነት ፀንተን እነዚህንና ሌሎችንም ሰው ተኮር ተግባራቶችን በጋራ ትብብር እንድናስቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ!!! በዚህ ታሪካዊ ተግባር ፈር ቀሳጅ በመሆን አሻራችሁን ላሳረፋችሁየሴትነትና የጥንካሬ ተምሳሌት ተስፋ ብርሃን በሃሳብ አመንጭነት እስከ ትግበራ በመሪነት የመሩና እየመሩ ያሉ ክብርት ዶ/ር አዳነች አቤቤ ሌሎች መሪዎቻችን መጋቢ እናቶች ፤ለድጋፍ አድራጊ ባለሃብቶች እና በየደረጃው ለምትመሩ እና ለምታስተባብሩ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለው መሪዎቻችን፣ መጋቢ እናቶች፣ ለድጋ አድራጊዎች እና ይህንን ተግባር በየደረጃው ለምትመሩ እና ለምታስተባብሩ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡