Publications

Megazine

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ 5 ዓመት በፊት በሀገራችን በተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እና ህብረ- ብሔራዊ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ ምስረታን ተከትሎ በርካታ የለውጥና የሪፎርም ስራዎችን በማካሄድ ቅድሚያ ሰው ተኮር ለሆኑ የልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት አብዛኛውን በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደር የከተማችንን ነዋሪ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች ተጠቃሚ እያደረገ መቆየቱ ይታወቃል። ከእነዚህ ከተከናወኑ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት መካከል በአብዛኛው ነዋሪ ዘንድ ተቀባይነትና ዕውቅና ያገኘው ተግባር በምገባ ኤጀንሲ አማካኝነት በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በቀን 2 ጊዜ ቁርስና ምሳ ዓመቱን ሙሉ የሚሰጠው የምገባ አገልግሎትና የተማሪዎች ደንብ ልብስ፤ የት/ት መርጃ ግብዓት አቅርቦት ስራ በዋናነት የሚጠቀስ ተግባር ነው። የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው ቁርጠኛ የፖለቲካ ውሳኔ መሰረት ወጪው ሙሉ በሙሉ በመንግሰት በጀት እየተሸፈነ አገልግሎቱ መሰጠት ከተጀመረበት ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በኤጀንሲው የቀረቡ የተማሪዎች ደንብ ልብስ፤ ደብተር፤ ጫማ፤ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፤ የመምህራን ጋዋን፤ የመጋቢ እናቶች ማብሰያ ሽርጥ፤ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን 452ሺ የነበረው የተማሪዎች ቁጥር ወደ ከ803 ሺበላይ፤ የመምህራን ቁጥር ከ28ሺ ወደ 37 ሺ በላይ፤ እንዲሁም የመጋቢ እናቶች ቁጥር ከ10ሺ ወደ ከ16ሺ በላይ ጨምሮ አገልግሎቱ እየቀረበ ሲሆን አገልግሎቱን ለማቅረብ የወጣው ወጪም በተመሳሳይ ወደ 2 ቢሊዮን ብር ደርሷል።